መዝሙር 104:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ክብርንና ግርማን ለብሰሃል።

2. ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል፤ሰማያትንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፤

3. የእልፍኝህን አግዳሚ በውሆች ላይ አኖርህ፤ደመናትን ሠረገላህ አደረግህ፤በነፋስ ክንፍ ትሄዳለህ።

4. መላእክትህን መንፈስ፣አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ።

5. ለዘላለም እንዳትናወጥ፣ምድርን በመሠረቷ ላይ አጸናሃት።

መዝሙር 104