መዝሙር 103:7-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. መንገዱን ለሙሴ፣ሥራውንም ለእስራኤል ሕዝብ አሳወቀ።

8. እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፣ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩም የበዛ ነው።

9. እርሱ ሁል ጊዜ በደልን አይከታተልም፤ለዘላለምም አይቈጣም።

10. እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤እንደ በደላችንም አልከፈለንም።

11. ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት።

12. ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ።

13. አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።

14. እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ትቢያ መሆናችንንም ያስባል።

15. ሰው እኮ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤እንደ ዱር አበባ ያቈጠቍጣል፤

16. ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ግን ድራሹ ይጠፋል፤ምልክቱም በቦታው አይገኝም።

17. የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤

መዝሙር 103