18. ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጉት ላይ ይሆናል።
19. እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል፤መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።
20. እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክቱ፤ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኀያላን፤ እግዚአብሔርን ባርኩ።
21. እናንተ ፈቃዱን የምትፈጽሙ አገልጋዮቹ፤ሰራዊቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ።
22. እናንተ በግዛቱ ሁሉ የምትኖሩ፣ፍጥረቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ፤ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።