መዝሙር 103:13-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።

14. እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ትቢያ መሆናችንንም ያስባል።

15. ሰው እኮ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤እንደ ዱር አበባ ያቈጠቍጣል፤

16. ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ግን ድራሹ ይጠፋል፤ምልክቱም በቦታው አይገኝም።

17. የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤

18. ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጉት ላይ ይሆናል።

19. እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል፤መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።

መዝሙር 103