መዝሙር 103:10-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤እንደ በደላችንም አልከፈለንም።

11. ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት።

12. ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ።

13. አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።

14. እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ትቢያ መሆናችንንም ያስባል።

15. ሰው እኮ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤እንደ ዱር አበባ ያቈጠቍጣል፤

መዝሙር 103