1. ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪየውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ።
2. ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤
3. ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣
4. ሕይወትሽን ከጥፋት ጒድጓድ የሚያድን፣ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣
5. ጐልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።
6. እግዚአብሔር ለተጨቈኑ ሁሉ፣ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣቸዋል።
7. መንገዱን ለሙሴ፣ሥራውንም ለእስራኤል ሕዝብ አሳወቀ።
8. እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፣ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩም የበዛ ነው።
9. እርሱ ሁል ጊዜ በደልን አይከታተልም፤ለዘላለምም አይቈጣም።