መዝሙር 102:26-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ።

27. አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።

28. የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።

መዝሙር 102