መዝሙር 102:21-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤

22. ይህም፣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣ እግዚአብሔርን ለማምለክ በአንድነት ሲሰበሰቡ ይሆናል።

23. ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤ዕድሜዬንም ባጭሩ አስቀረው።

24. እኔም እንዲህ አልሁ፤“አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ።

መዝሙር 102