መዝሙር 102:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ።

2. በመከራዬ ቀን፣ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ።

3. ዘመኔ እንደ ጢስ ተኖ አልቆአልና፤ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።

4. ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቆአል፤እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።

5. ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋር ተጣበቀ።

6. የምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጒጒት ሆንሁ።

7. ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤በቤቴ ጒልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።

መዝሙር 102