3. ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል።
4. ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤
5. መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው።በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል።
6. በልቡም፣ “ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም፤ከትውልድ እስከ ትውልድም መከራ አያገኘኝም” ይላል።
7. አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ።
8. በየመንደሩ ሥርቻ ያደፍጣል፤ንጹሐንን በሰዋራ ስፍራ ይገድላል።ዐይኖቹንም በምስኪኖች ላይ ያነጣጥራል።
9. በደኑ ውስጥ እንዳለ አንበሳ በስውር ያደባል፤ረዳት የሌለውን ለመያዝ ያሸምቃል፤ድኻውንም አፈፍ አድርጎ በወጥመዱ ይጐትታል።
10. ምስኪኑም ይደቃል፤ ዐንገቱን ይደፋል፤ያልታደለውም በክንዱ ሥር ይወድቃል።
11. በልቡም፣ “እግዚአብሔር ረስቶአል፤ፊቱን ሸፍኖአል፤ ፈጽሞም አያይም”ይላል።
12. እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ አምላክ ሆይ፤ ክንድህን አንሣ፤ረዳት የሌላቸውንም አትርሳ።