መዝሙር 10:2-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ።

3. ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል።

4. ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤

5. መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው።በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል።

6. በልቡም፣ “ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም፤ከትውልድ እስከ ትውልድም መከራ አያገኘኝም” ይላል።

7. አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ።

8. በየመንደሩ ሥርቻ ያደፍጣል፤ንጹሐንን በሰዋራ ስፍራ ይገድላል።ዐይኖቹንም በምስኪኖች ላይ ያነጣጥራል።

መዝሙር 10