መክብብ 9:11-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፡ሩጫ ለፈጣኖች፣ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤እንጀራ ለጥበበኞች፣ወይም ባለጠግነት ለብልሆች፣ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።

12. ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።

13. እንዲሁም እጅግ ያስገረመኝን ይህን የጥበብ ምሳሌ ከፀሓይ በታች አየሁ፦

14. ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኀያል ንጉሥም መጣባት፤ ከበባት፤ በላይዋም ትልቅ ምሽግ ሠራባት።

15. በዚያችም ከተማ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ይኖር ነበር፤ በጥበቡም ከተማዋን አዳናት፤ ነገር ግን ያን ድኻ ማንም አላስታወሰውም።

16. ስለዚህ፣ “ጥበብ ከኀይል ይበልጣል” አልሁ፤ ሆኖም የድኻው ጥበብ ተንቆአል፤ ቃሉም አልተሰማም።

17. ሞኞችን ከሚያስተዳድር ገዥ ጩኸት ይልቅ፣ጠቢብ በዝግታ የሚናገረው ቃል ይደመጣል።

መክብብ 9