መክብብ 8:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የሰው መከራ እጅግ ቢጫነውም፣ለሁሉም ነገር ትክክለኛ ጊዜና ተገቢ አሠራር አለው።

7. ሰው የወደ ፊቱን ስለማያውቅ፣ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል?

8. ሰው ነፋስን መቈጣጠር አይችልም፤በዕለተ ሞቱም ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፤በጦርነት ጊዜ ማንም ከግዴታ ነጻ እንደማይሆን፣ክፋትም የሚለማመዷትን አትለቃቸውም።

9. ከፀሓይ በታች የተሠራውን ሁሉ በአእምሮዬ መርምሬ፣ ይህን ሁሉ አየሁ። ሰው ሰውን ለመጒዳት ገዥ የሚሆንበት ጊዜ አለ።

መክብብ 8