መክብብ 4:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

5. ሰነፍ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል፤የገዛ ራሱንም ሥጋ ይበላል።

6. በድካምና ነፋስን በመከተል ከሚገኝ ሁለት ዕፍኝ ይልቅ፣በርጋታ የሚገኝ አንድ ዕፍኝ ይሻላል።

መክብብ 4