መክብብ 10:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፤ይህም ከገዥ የሚወጣ ስሕተት ነው፤

6. ሞኞች በብዙ የክብር ስፍራዎች ሲቀመጡ፣ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ስፍራ ሆነዋል።

7. መሳፍንት እንደ ባሮች በእግራቸው ሲሄዱ፣ባሮች ፈረስ ላይ ተቀምጠው አይቻለሁ።

8. ጒድጓድን የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ቅጥርንም የሚያፈርስ እባብ ይነድፈዋል።

መክብብ 10