2. የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ፣የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራ ያዘነብላል።
3. ሞኝ በጐዳና ሲሄድ ማስተዋል ይጐድለዋል፤ጅል መሆኑንም ለማንም ይገልጻል።
4. የገዥ ቊጣ በተነሣብህ ጊዜ፣ስፍራህን አትልቀቅ፤ትዕግሥት ታላቁን ጥፋት ጸጥ ያደርጋልና።
5. ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፤ይህም ከገዥ የሚወጣ ስሕተት ነው፤
6. ሞኞች በብዙ የክብር ስፍራዎች ሲቀመጡ፣ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ስፍራ ሆነዋል።
7. መሳፍንት እንደ ባሮች በእግራቸው ሲሄዱ፣ባሮች ፈረስ ላይ ተቀምጠው አይቻለሁ።