መክብብ 10:13-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ቃሉ በመጀመሪያ ሞኝነት ነው፤በመጨረሻም ደግሞ ክፉ እብደት ነው፤

14. ሞኙም ቃልን ያበዛል።የሚመጣውን የሚያውቅ የለም፤ከእርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ማን ሊነግረው ይችላል?

15. የሞኝ ሥራ ራሱን ያደክመዋል፤ወደ ከተማ የሚወስደውንም መንገድ አያውቅም።

16. አንቺ፣ ንጉሥሽ ልጅ የሆነ፣መሳፍንትሽም በጠዋት ግብዣ የሚያደርጉ ምድር ሆይ፤ ወዮልሽ!

17. አንቺ ንጉሥሽ ከተከበረው ዘር የሆነ፣ለመስከር ሳይሆን ለብርታት፣በተገቢው ጊዜ የሚበሉ መሳፍንት ያሉሽ ምድር ሆይ፤ የተባረክሽ ነሽ፤

18. ሰው ሰነፍ ከሆነ ጣራው ይዘብጣል፤እጆቹም ካልሠሩ ቤቱ ያፈሳል።

19. ግብዣ ለሣቅ ያዘጋጃል፤ወይንም ሕይወትን ያስደስታል፤ገንዘብም ካለ ሁሉ ነገር አለ።

መክብብ 10