መክብብ 10:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የሞቱ ዝንቦች ሽቶን እንደሚያገሙ፣ትንሽ ሞኝነትም ጥበብንና ክብርን ያቀላል።

2. የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ፣የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራ ያዘነብላል።

3. ሞኝ በጐዳና ሲሄድ ማስተዋል ይጐድለዋል፤ጅል መሆኑንም ለማንም ይገልጻል።

4. የገዥ ቊጣ በተነሣብህ ጊዜ፣ስፍራህን አትልቀቅ፤ትዕግሥት ታላቁን ጥፋት ጸጥ ያደርጋልና።

5. ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፤ይህም ከገዥ የሚወጣ ስሕተት ነው፤

መክብብ 10