መሳፍንት 5:30-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. ‘ምርኮ አግኝተው እየተከፋፈሉ፣እያንዳንዱም ሰው አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረዶች እየወሰደ አይደለምን?ይህ ሁሉ ምርኮ፣ በቀለም ያጌጡ ልብሶችለሲሣራ ደርሰውት፣በጌጣጌጥ የተጠለፉ ልብሶች ለአንገቴይዞልኝ እየመጣ አይደለምን?’

31. “እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤አንተን የሚወዱህ ግን፣ የንጋት ፀሐይበኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።”ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።

መሳፍንት 5