3. “እናንት ነገሥታት ይህን ስሙ፤ገዦችም አድምጡ፤ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ደግሜምለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ።
4. “እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ።
5. ተራሮች በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፣በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተናወጡ።
6. “በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ።
7. ለእስራኤል እናት ሆኜእኔ ዲቦራ እስክነሣ ድረስበእስራኤል ያለው የከተማ ኑሮ አበቃለት፤
8. አዳዲስ አማልክትን በተከተሉ ጊዜ፣ጦርነት እስከ ከተማው በር መጣ፤ጋሻም ሆነ ጦር፣በአርባ ሺህ እስራኤላውያን መካከል አልተገኘም።
9. ልቤ ከእስራኤል መሳፍንት፣ፈቃደኞችም ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው፤እግዚአብሔር ይመስገን።
10. “እናንት በነጫጭ አህዮች የምትጋልቡ፣በባለ ግላስ ኮርቻ ላይ የምትቀመጡ፣በመንገድ ላይ የምትጓዙ፣በውሃ ምንጮች ዙሪያ ያለውን፣
11. የዝማሬ ድምፅ ስሙ።ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል።“ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ወደ ከተማዪቱ በሮች ወረዱ፤
12. ‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤የአቢኒኤል ልጅ ባራቅ ሆይ፤ ተነሣ፤ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ።
13. የቀሩትም ሰዎች፣ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ እንደ ኀያል ጦረኛ ወደ እኔ መጣ።
14. መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶችከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋር ነበር፤የጦር አዛዥች ከማኪር፣የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ።
15. የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላውበመከተል፣ ከባርቅ ጋር ነበረ።በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር።
16. በበጎች ጒረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ?መንጎችን የሚጠራውን ፉጨት ለመስማት ነውን?በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር።
17. ገለዓድ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ዘገየ?አሴር በጠረፍ ቀረ፤በባሕሩ ዳርቻም ተቀመጠ።
18. የዛብሎን ሰዎች ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡየንፍታሌም ሰዎች እንደዚሁ በምድሪቱ ኰረብታዎች አደረጉ።
19. “ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤የከነዓን ነገሥታት፣ በመጊዶ ውሆች”አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፤ብርም ሆነ ሌላ ምርኮ ተሸክመው አልሄዱም።
20. ከሰማያት ከዋክብት ተዋጉ፤በአካሄዳቸውም ሲሣራን ገጠሙት።
21. ጥንታዊው ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ፣የቂሶን ወንዝ ጠርጐ ወሰዳቸው፤ነፍሴ ሆይ፤ በኀይል ገሥግሺ
22. የፈረሶች ኮቴ ድምፅ በኀይል ተሰማ፤ጋለቡ፤ በኀይልም ፈጥነው ጋለቡ።