መሳፍንት 5:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. በበጎች ጒረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ?መንጎችን የሚጠራውን ፉጨት ለመስማት ነውን?በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር።

17. ገለዓድ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ዘገየ?አሴር በጠረፍ ቀረ፤በባሕሩ ዳርቻም ተቀመጠ።

18. የዛብሎን ሰዎች ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡየንፍታሌም ሰዎች እንደዚሁ በምድሪቱ ኰረብታዎች አደረጉ።

መሳፍንት 5