መሳፍንት 5:13-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. የቀሩትም ሰዎች፣ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ እንደ ኀያል ጦረኛ ወደ እኔ መጣ።

14. መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶችከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋር ነበር፤የጦር አዛዥች ከማኪር፣የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ።

15. የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላውበመከተል፣ ከባርቅ ጋር ነበረ።በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር።

16. በበጎች ጒረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ?መንጎችን የሚጠራውን ፉጨት ለመስማት ነውን?በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር።

17. ገለዓድ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ዘገየ?አሴር በጠረፍ ቀረ፤በባሕሩ ዳርቻም ተቀመጠ።

18. የዛብሎን ሰዎች ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡየንፍታሌም ሰዎች እንደዚሁ በምድሪቱ ኰረብታዎች አደረጉ።

19. “ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤የከነዓን ነገሥታት፣ በመጊዶ ውሆች”አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፤ብርም ሆነ ሌላ ምርኮ ተሸክመው አልሄዱም።

20. ከሰማያት ከዋክብት ተዋጉ፤በአካሄዳቸውም ሲሣራን ገጠሙት።

21. ጥንታዊው ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ፣የቂሶን ወንዝ ጠርጐ ወሰዳቸው፤ነፍሴ ሆይ፤ በኀይል ገሥግሺ

22. የፈረሶች ኮቴ ድምፅ በኀይል ተሰማ፤ጋለቡ፤ በኀይልም ፈጥነው ጋለቡ።

መሳፍንት 5