መሳፍንት 5:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤የአቢኒኤል ልጅ ባራቅ ሆይ፤ ተነሣ፤ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ።

13. የቀሩትም ሰዎች፣ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ እንደ ኀያል ጦረኛ ወደ እኔ መጣ።

14. መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶችከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋር ነበር፤የጦር አዛዥች ከማኪር፣የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ።

15. የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላውበመከተል፣ ከባርቅ ጋር ነበረ።በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብምርምር ነበር።

መሳፍንት 5