መሳፍንት 5:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚያን ዕለት ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህን ቅኔ ተቀኙ፤

2. “በእስራኤል ያሉ መሳፍንት ሲመሩ፣ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ።

3. “እናንት ነገሥታት ይህን ስሙ፤ገዦችም አድምጡ፤ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ደግሜምለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ።

መሳፍንት 5