መሳፍንት 21:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ብንያማውያን እንደ ተባሉት አደረጉ፤ ልጃገረዶቹ በሚጨፍሩበትም ጊዜ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እየጠለፈ ሚስት እንድትሆነው ይዞ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ርስታቸው ተመለሱ፤ ከተሞቻቸውንም አድሰው በዚያ ኖሩ።

24. በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ያን ቦታ ትተው ወደየቤታቸው፣ ወደየርስታቸው፣ ወደየጐሣቸውና ወደየነገዳቸው ሄዱ።

25. በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።

መሳፍንት 21