መሳፍንት 18:26-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. የዳን ሰዎች ይህን ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሚካም የማይችላቸው መሆኑን በማየት ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ።

27. ከዚያም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወስደው ወደ ላይሽ በመሄድ፣ በሰላምና ያለ ስጋት ይኖር የነበረውን ሕዝብ በሰይፍ መቱት፤ ከተማዪቱንም በእሳት አቃጠሏት።

28. የሚኖሩት ከሲዶና በጣም ርቀው ስለ ነበርና ከማንም ጋር ግንኙነት ስላልነበራቸው የሚታደጋቸው አንድም አልነበረም፤ ከተማዪቱም የምትገኘው በቤትሮዓብ አጠገብ ነበረ።የዳንም ሰዎች ከተማዪቱን እንደ ገና ሠርተው መኖሪያቸው አደረጓት።

መሳፍንት 18