መሳፍንት 17:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ስለዚህ ሌዋዊው አብሮት ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት።

12. ሚካም ሌዋዊውን ካህን አድርጎ አስቀመጠው፤ ወጣቱም ካህኑ ሆነ፤ በቤቱም ኖረ።

13. ሚካም፤ “ይህ ሌዋዊ ካህን ለሆነልኝ፣ እግዚአብሔር በጎ ነገር እንደሚያደርግልኝ አሁን ተረዳሁ” አለ።

መሳፍንት 17