ሕዝቅኤል 7:13-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ሁለቱ በሕይወት እስካሉ ድረስ ሻጩ የሸጠውን መሬት አያስመልስም፤ ስለ መላው ሕዝብ የተነገረው ራእይ አይለወጥምና። ከኀጢአታቸው የተነሣ ሕይወቱን ማትረፍ የሚችል አንድም አይገኝም።

14. መለከት ቢነፉም፣ ሁሉንም ነገር ቢያዘጋጁም፣ ወደ ጦርነት የሚሄድ አንድ እንኳ አይኖርም፤ መዓቴ በሕዝብ ሁሉ ላይ መጥቶአልና።

15. “በውጭ ሰይፍ፣ በውስጥ ደግሞ ቸነፈርና ራብ አለ፤ በገጠር ያሉት በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በከተማ ያሉትም በራብና በቸነፈር ያልቃሉ።

16. ተርፈው ያመለጡት ሁሉ በሸለቆ እንደሚኖሩ ርግቦች ስለ ኀጢአታቸው እያለቀሱ በተራራ ላይ ይሆናሉ።

ሕዝቅኤል 7