ሕዝቅኤል 42:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ወርዱ ዐሥር ክንድ፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ የሆነ መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበር። የክፍሎቹም በሮች በሰሜን በኩል ነበሩ።

5. የላይኞቹ ክፍሎች ጠበብ ያሉ ናቸው፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ታችና መካከል ላይ ካሉት ከሕንጻው ክፍሎች ይልቅ ሰፋ ያሉ ቦታዎች ይዘውባቸዋልና።

6. አደባባዮቹ ዐምዶች ሲኖሯቸው፣ በሦስተኛው ደርብ ላይ ያሉት ክፍሎች ግን ዐምድ የላቸውም። ስለዚህ የወለላቸው ስፋት በታችኛውና በመካከለኛው ደርብ ካሉት ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያለ ነው።

7. ከክፍሎቹና፣ ከውጩ አደባባይ ትይዩ የሆነ የውጪ ግንብ አለ፤ ይህም በክፍሎቹ ፊት ለፊት ሆኖ አምሳ ክንድ ይረዝማል።

8. ከውጩ አደባባይ ቀጥሎ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት አምሳ ክንድ ሲሆን፣ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ነበር።

9. ከውጩ አደባባይ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ በስተ ምሥራቅ የታችኞቹ ክፍሎች መግቢያ ይገኛል።

ሕዝቅኤል 42