ሕዝቅኤል 31:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖንና ስፍር ቍጥር ለሌለው ሕዝቡ እንዲህ በል፤“ ‘በክብር ከአንተ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል፤

3. ለጫካው ጥላ የሆኑ የሚያማምሩ ቅርንጫፎች የነበሩትን፣እጅግ መለሎ ሆኖ፣ጫፉ ሰማይ የደረሰውን፣የሊባኖስን ዝግባ አሦርን ተመልከት።

ሕዝቅኤል 31