5. ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ልድያና መላው ዐረብ፣ ሊብያና የቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብፅ ጋር በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።
6. “ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘የግብፅ ተባባሪዎች ይወድቃሉ።የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል።ከሚግዶል እስከ አስዋን፣በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
7. “ ‘በባድማ መሬቶች መካከል፣ባድማ ይሆናሉ፤ከተሞቻቸውም፣ከፈራረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ።
8. በግብፅ ላይ እሳት ስጭር፣ረዳቶቿ ሁሉ ሲደቁ፣በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ፤
9. “ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ተዘልላ ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብፅ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በእርግጥ ይመጣልና።