ሕዝቅኤል 29:19-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ግብፅን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጣለሁ፤ ሀብቷን ሁሉ ያግዛል፤ ለሰራዊቱም ደመወዝ ይሆን ዘንድ ምድሪቱን ይበዘብዛል፤ ይመዘብራልም።

20. እርሱና ሰራዊቱ ለእኔ በመልፋታቸው፣ ግብፅን ለድካሙ ዋጋ ሰጥቼዋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

21. “በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድ አበቅላለሁ፤ በመካከላቸውም አፍህን እከፍታለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።

ሕዝቅኤል 29