3. ከዳንኤል ይልቅ ጠቢብ ነህን?ከአንተስ የተሰወረ ምስጢር የለምን?
4. በጥበብህና በማስተዋልህ፣የራስህን ሀብት አከማቸህ፤ወርቅም ብርም፣በግምጃ ቤትህ አጠራቀምህ።
5. በንግድ ሥራ እጅግ ከመራቀቅህ የተነሣ፣በሀብት ላይ ሀብት አካበትህ፤ከሀብትህ ብዛት የተነሣም፤ልብህ በትዕቢት ተወጠረ።
6. “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘እንደ አምላክ ጥበበኛ ነኝ፤ ብለህስለምታስብ፣
7. ከአሕዛብ መካከል እጅግ ጨካኞች የሆኑትን ባዕዳን፣በአንተ ላይ አመጣለሁ፤በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ታላቅ ክብርህንም ያረክሳሉ።
8. ወደ ጒድጓድ ያወርዱሃል፤በጥልቁም ባሕር ውስጥ፣በባሕሮችም ልብ ውስጥ አስከፊ ሞት ትሞታለህ።