ሕዝቅኤል 27:24-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. እነዚህም በገበያሽ ውስጥ ያማረ ልብስ፣ ሰማያዊ ካባ፣ ወርቀ ዘቦ እንዲሁም በኅብረ ቀለም ያሸበረቀና በጥብቅ የተታታ ስጋጃ በማቅረብ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር።

25. “ ‘የተርሴስ መርከቦች፣ሸቀጥሽን አጓጓዙልሽ፤በባሕር መካከልም፣በከባድ ጭነት ተሞልተሽ ነበር።

26. ቀዛፊዎችሽ፣ወደ ጥልቁ ባሕር ይወስዱሻል፤የምሥራቁ ነፋስ ግን፣በባሕሩ መካከል ይሰባብርሻል።

27. የመርከብ አደጋ በሚደርስበሽ ቀን፣ሀብትሽ፣ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃሽ፣መርከብ ነጂዎችሽ፣ መርከበኞችሽና መርከብ ሠሪዎችሽ፣ነጋዴዎችሽና ወታደሮችሽ ሁሉ፣በመርከብ ላይ ያሉትም ሁሉ፣ወደ ባሕሩ ወለል ይዘቅጣሉ።

ሕዝቅኤል 27