1. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ስለ ጢሮስ ሙሾ አውርድ፤
3. በባሕር መግቢያ ላይ ለምትገኘውና በብዙ ጠረፎች ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ለምትነግደው ለጢሮስ እንዲህ በላት፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ጢሮስ ሆይ!፤“ፍጹም ውብ ነኝ” ብለሻል፤
4. ዳርቻሽ በባሕር መካከል ነው፤ሠሪዎችሽም ፍጹም ውብ አድርገውሻል።
5. ሳንቃዎችሽን ሁሉ፣ከሳኔር በመጣ ጥድ ሠሩ፤ደቀልንም ይሠሩልሽ ዘንድ፤ከሊባኖስ ዝግባ አመጡ።
6. ከባሳን በመጣ ወርካ፣መቅዘፊያሽን ሠሩ፤ከቆጵሮስ ጠረፍ በመጣ ዝግባ፣በዝኆን ጥርስ ለብጠው ወለልሽን ሠሩ።