ሕዝቅኤል 26:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ! ጢሮስ ስለ ኢየሩሳሌም፣ ‘እሰይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች፤ ደጆቿም ወለል ብለው ተከፈቱልኝ፤ እንግዲህ እርሷ ስለ ፈራረሰች እኔ እከብራለሁ’ ብላለችና፤

3. ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ጢሮስ ሆይ፤ እነሆ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ባሕር ሞገዷን እንደምታስነሣ፣ ብዙ ሕዝብ አስነሣብሻለሁ።

4. የጢሮስን ቅጥሮች ያወድማሉ፤ ምሽጎቿንም ያፈርሳሉ። ዐፈሯን ከላይዋ ጠርጌ የተራቈተ ዐለት አደርጋታለሁ።

5. እኔ ልዑል እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፤ በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆናለች፤ አሕዛብም ይበዘብዟታል፤

6. መኻል አገር ያሉ ሰፈሮቿም በሰይፍ ይወድማሉ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።

7. “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሠረገሎች ጋር፣ ከፈረሰኞችና ከታላቅ ሰራዊትም ጋር ከሰሜን በጢሮስ ላይ አመጣለሁ።

8. እርሱ መኻል አገር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማቸዋል፤ በዙሪያሽ ካብ ይክባል፤ እስከ ቅጥሮችሽ ጫፍ ድረስ ዐፈር ይደለድ ልብሻል፤ ጋሻውንም በአንቺ ላይ ያነሣል።

ሕዝቅኤል 26