ሕዝቅኤል 23:33-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፣በመፍረስና በጥፋት ጽዋ፣በስካርና በሐዘን ትሞዪአለሽ።

34. ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽም፤ከዚያም ጽዋውን ትሰባብሪዋለሽ፤ጡትሽንም ትቈራርጪአለሽ፤እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

35. “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ረስተሽኛል፤ ወደ ኋላም ገሸሽ አድርገሽኛልና የብልግናሽንና የሴሰኝነትሽን ውጤት ትሸከሚአለሽ።’

36. እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ ጸያፍ ተግባራቸውን ንገራቸው።

ሕዝቅኤል 23