15. በሕዝቦች መካከል እበትንሻለሁ፤ በየአገሩም እዘራሻለሁ፤ ከርኵሰትሽም አጠራሻለሁ።
16. በሕዝቦች ዘንድ በምትረክሺበት ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቂያለሽ።’ ”
17. የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
18. “የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት የብረት ዝቃጭ ሆነብኝ፤ ሁሉም በከውር ውስጥ ቀልጦ እንደሚቀር መዳብ፣ ቈርቈሮ፣ ብረትና እርሳስ ናቸው፤ እነዚህ ከብር የሚወጡ ዝቃጭ ናቸው።
19. ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ሁላችሁም የብረት ዝቃጭ ስለ ሆናችሁ ወደ ኢየሩሳሌም እሰበስባችኋለሁ።