8. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
9. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሰይፍ! ሰይፍ!የተሳለ የተወለወለም፤
10. የተሳለው ሊገድል፣የተወለወለውም እንደ መብረቅ ሊብረቀረቅ ነው!“ ‘ታዲያ፣ እንዴት ደስ ሊለን ይችላል? ሰይፉ የልጄን በትረ መንግሥት እንደ ማንኛውም በትር ንቆአል።
11. “ ‘በእጁ እንዲያዝ፣ሰይፉ ሊወለወል ተሰጥቶአል፤ገዳዩ በእጁ እንዲጨብጠው፣ተስሎአል፤ ተወልውሎአል።
12. የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህ በሕዝቤ ላይ፣በእስራኤልም መሳፍንት ሁሉ ላይ መጥቶአልና፤ጩኸት፣ ዋይታም አሰማ።እነርሱ ከሕዝቤ ጋር በአንድ ላይ፣ለሰይፍ ተጥለዋል፤ስለዚህ ደረትህን ምታ።