ሕዝቅኤል 12:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. በዙሪያው ያሉትን ረዳቶቹንና ወታደሮቹን ሁሉ ወደ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፤ በተመዘዘም ሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።

15. “በአሕዛብ መካከል ስበትናቸውና በአገሮችም መካከል ስዘራቸው፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።

16. ነገር ግን በሄዱባቸው አሕዛብ መካከል ስለ ጸያፍ ተግባራቸው ይናገሩ ዘንድ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ከሰይፍ ከራብና ከቸነፈር አተርፋለሁ። በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።”

17. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

ሕዝቅኤል 12