16. “ስለዚህ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በአሕዛብ መካከል ብሰድዳቸውም፤ በአገሮች መካከል ብበታትናቸውም፣ በሄዱባቸው አገሮች ሁሉ ለጥቂት ጊዜ መቅደስ ሆኜአቸዋለሁ’ ”።
17. “ስለዚህ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከአሕዛብ መካከል እሰበስባችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸው አገሮች እመልሳችኋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እንደ ገና እሰጣችኋለሁ።”
18. “ወደዚያ በተመለሱ ጊዜ የረከሱ ምስሎቿንና ጸያፍ ተግባሯን ያስወግዳሉ።