ሐዋርያት ሥራ 8:32-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. ጃንደረባው ያነብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤“እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤የበግ ጠቦት በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፣እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

33. ራሱን በማዋረዱም ፍትሕን ተነፈገ፤ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና፣ስለ ትውልዱ ማን ሊናገር ይችላል?”

34. ጃንደረባውም መልሶ ፊልጶስን፣ “ነቢዩ ይህን የሚናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነው፣ ወይስ ስለ ሌላ ሰው? እባክህ ንገረኝ” አለው።

35. ፊልጶስም አፉን ከፈተ፤ ከዚሁም መጽሐፍ ክፍል ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌል ሰበከለት።

36. በመጓዝ ላይ ሳሉም ውሃ ካለበት ስፍራ ደረሱ፤ ጃንደረባውም፣ “እነሆ፤ ውሃ እዚህ አለ፤ ታዲያ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?” አለው።

ሐዋርያት ሥራ 8