ሐዋርያት ሥራ 24:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በየቦታውና በየጊዜው ይህን ውለታ በታላቅ ምስጋና እንቀበላለን።

4. ነገር ግን ይበልጥ እንዳላደክምህ፣ በአጭሩ እንድ ትሰማን መልካም ፈቃድህን እለምንሃለሁ።

5. “ይህ ሰው፣ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ መካከል በሽታ ሆኖ ሁከት የሚያስነሣ፣ ደግሞም የናዝራውያን ወገን ቀንደኛ መሪ ሆኖ አግኝተነዋል።

6. ከዚህም በላይ ቤተ መቅደሱን ለማርከስ ሲሞክር አግኝተን ያዝነው። በሕጋችንም መሠረት ልንፈርድበት አስበን ነበር፤

7. ነገር ግን የጦር አዛዡ ሉስዮስ መጥቶ በታላቅ ኀይል ከእጃችን ነጥቆ ወሰደው፤ ከሳሾቹም ወደ አንተ እንዲመጡ አዘዘ።

ሐዋርያት ሥራ 24