23. እግዚአብሔር በጥንት ውሳኔውና በቀደመው ዕውቀቱ ይህን ሰው አሳልፎ በእጃችሁ ሰጣችሁ፤ እናንተም በክፉ ሰዎች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።
24. እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አስወግዶ አስነሣው፤ ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለምና።
25. ዳዊትም ስለ እርሱ እንዲህ ይላል፤“ ‘ጌታን ሁል ጊዜ በፊቴ አየዋለሁ፤እርሱ በቀኜ ነውና፣ከቶ አልታወክም።
26. ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤ሥጋዬም በተስፋ ይኖራል።
27. ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፤ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።
28. የሕይወትን መንገድ እንዳውቅ አደረግኸኝ፤በፊትህም በሐሤት ትሞላኛለህ።’
29. “ወንድሞች ሆይ፤ ከቀደምት አባቶች ዳዊት ሞቶ እንደ ተቀበረ፣ መቃብሩም እስከ ዛሬ ድረስ በመካከላችን እንደሚገኝ በድፍረት መናገር እችላለሁ።
30. ነቢይ በመሆኑም፣ እግዚአብሔር ከዘሮቹ አንዱን በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ በመሐላ ቃል የገባለት መሆኑን ዐወቀ።