ሐዋርያት ሥራ 12:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ሄሮድስም ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሰጠ የጌታ መልአክ ወዲያው መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።

24. የእግዚአብሔር ቃል ግን እያደገና እየሰፋ ሄደ።

25. በርናባስና ሳውልም ተልእኮአቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋር ይዘውት መጡ።

ሐዋርያት ሥራ 12