9. ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቤተ መቅደስ ጒልላት ላይ አቆመውና እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እስቲ ራስህን ከዚህ ወደ ታች ወርውር፤
10. ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤“ ‘ይጠብቁህ ዘንድ፣መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋል፤
11. እግርህም ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣በእጆቻቸው ወደ ላይ አንሥተው ይይዙሃል።’ ”
12. ኢየሱስም፣ “ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎአል” ብሎ መለሰለት።
13. ዲያብሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ከእርሱ ተለየ።
14. ኢየሱስም በመንፈስ ኀይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ዝናውም በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ ወጣ።
15. እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር ነበር፤ ሰውም ሁሉ ያመሰግነው ነበር።
16. ከዚያም ወዳደገበት ከተማ ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገባ፤ ሊያነብም ተነሥቶ ቆመ።
17. የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልል መጽሐፍም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም መጽሐፍ በተረተረው ጊዜ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ክፍል አገኘ፤