ሉቃስ 24:39-42 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

39. እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ እኔው ራሴ ነኝ። ደግሞም ንኩኝና እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና ዐጥንት የለውምና።”

40. ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው።

41. እነርሱም ከመደሰትና ከመገረም የተነሣ ገና ሳያምኑ፣ “በዚያ ቦታ አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁን?” አላቸው።

42. እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራሽ ሰጡት፤

ሉቃስ 24