ሉቃስ 22:66-69 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

66. በነጋም ጊዜ፣ የሕዝብ ሽማግሌዎች፣ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ተሰበሰቡ፤ ኢየሱስንም በሸንጎአቸው ፊት አቀረቡት።

67. እነርሱም፣ “አንተ ክርስቶስ ነህን? እስቲ ንገረን” አሉት።ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ብነግራችሁ አታምኑኝም፤

68. ብጠይቃችሁም አትመልሱም።

69. ነገር ግን ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ኀይል ቀኝ ይቀመጣል።”

ሉቃስ 22