ሉቃስ 10:41-42 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. ጌታ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ማርታ፣ ማርታ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትዋከቢአለሽም፤

42. የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም እኮ የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእርሷ አይወሰድም።”

ሉቃስ 10