55. ይህም ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፣ለአብርሃምና ለዘሩ ያለውን ለዘላለም ለመጠበቅ ነው።”
56. ማርያምም ሦስት ወር ያህል ኤልሳቤጥ ዘንድ ከቈየች በኋላ ወደ ቤቷ ተመለሰች።
57. የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ቀን ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለደች።
58. ጎረቤቶቿና ዘመ ዶቿም ጌታ ታላቅ ምሕረት እንዳደረገላት ሰሙ፤ የደስታዋም ተካፋዮች ሆኑ።
59. በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ፈለጉ፤
60. እናቱ ግን፣ “አይሆንም፤ ዮሐንስ መባል አለበት” አለች።
61. እነርሱም፣ “ከዘመዶችሽ በዚህ ስም የተጠራ ማንም የለም” አሏት።